የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2018 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከመሥሪያ ቤት አመራሮች፣ ከፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች እና ከቡድን መሪዎች ጋር ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት አካሂዷል።

በ2018 በጀት ዓመት ፕሮጀክቶችን በመምራት፣ በማስተዳደር እንዲሁም አጠናቆ ለምረቃ በማብቃት ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመረከብ፣ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማጠናከር ፋይናንሳዊ ጤናማነትን ለማረጋገጥ፣ የሀብት አጠቃቀምንና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እንዲሁም የሥራ አካባቢን ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የሰው ኃይል ልማትንና አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ፣ የማሽነሪና ተሽከርካሪ ጥገና አቅምን ለማሳደግ፣ ሥራዎችን አቀናጅቶ ለመሥራት እንዲሁም ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።

ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ ከመሆናቸውም ባሻገር፣ ለቀጣይ ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዘርፎች የተለዩበት ወቅት እንደነበር ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ጉድለቶች በማረም ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደሚገባና በሁሉም የሥራ ዘርፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።