የዘመኑን የቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ::

የዘመኑን የቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ::

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሰራሩን ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ የጀመረው የዲጂታላይዜሽን ጉዞ አካል የሆነው የተግባር ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ተቋሙ ካለበት ሰፊ ኃላፊነት አንጻር አሰራሮችን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሰራራችንን ከወረቀት ንክኪ ወደ ዲጂታል ማሸጋገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው በማለት፣ አመራሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንዲከተል ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በአፅንኦት ሰጥተዋል።

በአመራር ደረጃ የተጀመረው ስልጠና በተዋረድ እስከ ታችኛው የሥራ ክፍል ድረስ እንደሚቀጥልና ተቋሙ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል የሥራ አካባቢ ለመቀየር የያዘውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በኢንተርፕራይዙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት መምሪያ የተሰጠው ይህ ስልጠና፤ የሥራ መሪዎች የኢሜል ልውውጥንና የሥራ መርሃ-ግብር ምደባን በአውትሉክ (Outlook) መተግበሪያ፣ እንዲሁም የሥራ ሪፖርት አቀራረብን በሰርኩኒ (Serkuni) መተግበሪያ በኩል በዘመናዊ መንገድ እንዲመሩ ለማስቻል የታለመ ነው። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሚሳኤል የማነ እንደገለጹት፤ ስልጠናው አመራሩ መረጃዎችን በፍጥነት እንዲለዋወጥና ሥራዎችን በቅልጥፍና እንዲያከናውን ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

Stay Updated with DCE News

Subscribe to our newsletter and never miss an update about our projects, achievements, and announcements.