የመ.ኮ.ኢ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሆስፒታልን ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማጠናቀቅ ውል ተፈራረመ::

የመ.ኮ.ኢ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሆስፒታልን ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማጠናቀቅ ውል ተፈራረመ::

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያስገነባውን የፋሲሊቲ ሆስፒታል ቀሪ ሥራዎች ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያስገነባውን የፋሲሊቲ ሆስፒታል ቀሪ ሥራዎች ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ እና የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብ/ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ ውሉን በጋራ ፈርመዋል።

ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ፤ "የሆስፒታሉ ግንባታ ከ14 ዓመታት በላይ በመዘግየቱ፣ አሁን ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ጋር የተደረገው ስምምነት ግንባታውን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለታራሚዎችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።"

ብ/ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፦ "ኢንተርፕራይዙ በግዙፍ መሠረተ ልማቶች ላይ ያለውን ሰፊ ልምድ በመጠቀም፣ ይህን ሆስፒታል በተቀመጠለት የጊዜ ገደብና በላቀ ጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ቁርጠኛ ነው።"

በግንባታው የሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፡-
•  የቀሪ የሲቪል ሥራዎች ማጠናቀቂያ
•  ሙሉ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
•  የፍሳሽ እና የቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ (Treatment) እና የሳይት ወርክ ሥራዎች ናቸው፡፡

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ለታራሚዎችም ሆነ ለጠቅላላው ማኅበረሰብ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ይሆናል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና አማካሪ ድርጅቶች የሆስፒታሉን የግንባታ ደረጃ በመስክ ምልከታ ጎብኝተዋል።

Stay Updated with ECWC News

Subscribe to our newsletter and never miss an update about our projects, achievements, and announcements.